አርትስ 04/01/2011rnየቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሐመድ ጨምሮ የሌሎች ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ እየተመለከተ ያለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ተረኛ ምድብ ችሎት በተጠርጣሪዎች የቀረቡትን አቤቱታ ሰምቷል።rnኢቢሲ እንደዘገበው ተጠርጣሪዎቹ ቤተሰብ እየጠየቅን አይደለም ምግብና ህክምናም በአግባቡ እያገኘን አይደለም የሚል ቅሬታ በጠበቆቻቸው በኩል አቅርበዋል።rnመዝገቡ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች በአንድ የያዘ ነው እንደኃላፊነታችን መጠን ሊለያይ ይገባል ሲሉም ፤የዋስትና መብታቸውም እንዲከበር ጠይቀዋል ።<span class="text_exposed_show">rnፍርድ ቤቱ የቀረቡትን ጉዳዮች በተመለከተ ለፖሊስ ተገቢውን ማስተካከያ እንዲያደረግ ትዕዛዝ ሰጥቷል።rnየተጠረጠሩበት ወንጀል የዋስትና መብት ስለማያሰጣቸው ይህን ጥያቄ ውድቅ በማድርግ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።rnበመሆኑም ቀጣይ የቀጠሮ ጊዜ መስከረም 18 እንደሚሆን ፍርድቤቱ ወስኗል።</span>
← NewsLegal
ፖሊስ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ መሀመድን ጨምሮ በሌሎች ተከሳሾች ላይ የጠየቀው ተጨማሪ 14 ቀን የምርምራ ጊዜ በፍርድ ቤቱ ተፈቀደለት
Arts TV · ሴፕቴ 14 2018





