ኬንያ በሙስና የጠረጠረቻቸውን ባለ ስልጣኖቿን አሰረች፡፡rnrnአቃቤ ህግ ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርብለት ተጠርጣሪዎችን በስም ጠቅሶ መግለጫ መስጠቱን ተከትሎ የኬንያ የፋይናንስ ሚኒስትር እና የሀገሪቱ የአካባቢ ጥበቃ ሃላፊ እጃቸውን በፈቃዳቸው ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡rnrnአልጀዚራ እንደዘገበው ኬንያ በሙስና ወንጀል ተሳትፈዋል ያለቻቸውን 28 ባለ ስልጣኖቿን በቁጥጥር ስር አውላቸዋለች፡፡rnrnየኬንያ ፖሊስ ሀላፊ ጆርጅ ኪንቶቲ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት ከሆነ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣቂዎች በማረፊያ ቤት ሆነው ፍርድ ቤት የሚቀርቡበትን ጊዜ እየተጠባበቁ ነው፡፡rnrnኬንያ በታሪኳ በስልጣን ላይ ያሉ ሚስትሮቿን ስታስር የፋይናንስ ሚኒስትሩ ሄንሪ ሮቲች የመጀመሪያው ናቸው ተብሏል፡፡rnrnአቃቤ ህግ በሰጠው መግለጫ ሮቲች እና ተባባሪዎቻቸው በፈፀሟቸው ኢኮኖሚያዊ አሻጥሮች እስከ ስምንት የሚደርሱ ክሶች ይጠብቋቸዋል ብለዋል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ






