Arts TVArts TV
← NewsLegal

ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም አዋጅ አፀደቀች፡፡

Arts TV · ኤፕሪ 17 2019

ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም አዋጅ አፀደቀች፡፡

ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ አጠቃቀም አዋጅ አፀደቀች፡፡rnrnየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 33ኛ መደበኛ ስብሰባው የጦር መሳሪያ  አስተዳደር አዋጅ አፅድቋል፡፡rnrnየረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ  መስፍን ቸርነት የአገርና የህዝብን  ፀጥታ እና ሰላም ለማስጠበቅ ያለመ ነው ብለዋል፡፡rnrnግለሰቦች የታጠቋቸውን መሳሪዎች የሕብረተሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ተግባር ላይ እንዲያውሉ እንዲሁም ህገ-ወጥ የጦር መሳሪዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር እንደሚያስችልም አብራርተዋል፡፡rnrnበውይይቱ ወቅት የጦር መሳሪያ ፈቃድ የሚሰጣቸው አካላት መስፈርት በጣም ቀላል በመሆኑ ማንኛውም አካል ዝም ብሎ መሳሪያ እንዲታጠቅ በር አይከፍትም ወይ የሚል ጥያቄ ተነስቶም ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡rnrnመረጃው  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው፡፡

More in Legal