ናይጀሪያ በሴቶች ላይ ጥቃት የሚፈፅሙ ሰዎች ስማቸው በልዩ መዝገብ እንዲሰፍር ልታደርግ ነው፡፡rnrnአዲሱ አሰራር ከፆታ ጋር የተያያዘ ጥቃት አድራሾችን በዳታቤዝ መዝግቦ በማስቀመጥ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ለመከላከል ታስቦ ነው የተዘጋጀው ተብሏል፡፡rnrnአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው በዚህ የዳታቤዝ ሲስተም እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር ከ2015 ጀምሮ ፆታዊ ጥቃት አድርሰው የተከሰሱ እና የተቀጡ ሰዎች ስም ዝርዝር ይሰፍራል፡፡rnrnበናይጀሪያ ከ4 ሴቶች መካከል አንዷ 18 ዓመት ሳይሞላት ጾታዊ ጥቃት እንደሚደርስባት ዩኒሴፍጥናት ያሳያል፡፡rnrnይሁን እንጂ ከነዚህ ወንጀሎች መካከል አብዛኞቹ ለፖሊስ ሪፖርት ስለማይደረጉ አጥፊዎቹ ከመጥፎ ድርጊታቸው መቆጠብ አልቻሉም ይላል ጥናቱ፡፡rnrnየናይጀሪያ መንግስት ይህን ስትራቴጂ መዘርጋቱ ወደፊት ሴቶች ላይ ትንኮሳ እና ጥቃት ለማድረስ የሚያስቡ ግለሰቦች ምዝገባውን በመፍራት ይታቀባሉ የሚል እምነት አሳድሯል፡፡rnrnመንገሻ ዓሙ
← NewsLegal
ናይጀሪያ በሴቶች ላይ ጥቃት የሚፈፅሙ ሰዎች ስማቸው በልዩ መዝገብ እንዲሰፍር ልታደርግ ነው፡፡
Arts TV · ኖቬም 26 2019






