እስራኤል በድብቅ መሳሪያ ሲያጓጉዝ አገኘሁት ያለችውን ፈረንሳዊ በእስር ቀጣች፡፡rnrnሮሜይን ፍራንክ የተባለው ፈረንሳዊ ከጋዛ ወደ ዌስት ባንክ በድብቅ የጦር መሳሪያዎችን ሲያሸጋግር እንደተደረሰበት ፍርድ ቤት ቀርቦ በማመኑ በ7 ዓመት እንዲቀጣ ተወስኖበታል፡፡rnrnታይምስ ኦፍ እስራኤል እንደዘገበው ፍራንክ የእስር ቅጣቱ ቀላል የሆነለት መሳሪያውን ለፍልስጤማዊያን ሊያጓጉዝላቸው የተስማማው ንንዘብ ለማግኘት ሲል ብቻ መሆኑ ስለተረጋገጠ ነው፡፡rnrnተከሳሹ በሀገሩ ፈረንሳይ ቆንስላ ፅህፈት ቤት ሾፌር ሆኖ ሲያገለግል የዲፕሎማቲክ ተሽከርካሪ በመጠቀም 70 ሽጉጦችን እና 2 አውቶማቲክ ጠብመንጃዎችን ገንዘብ ተከፍሎት ሲያገጓጉዝ ነው በእስራኤል የፀጥታ ሰዎች የተያዘው፡፡rnrnየእሰራኤል አቃቤ ህግ ባሰባሰበው ማስረጃ ፍራንክ መሳሪያዎቹን ለፍልስጤማዊያን በማጓጓዝ 7 ሺህ 600 ዶላር እንደተከፈለው ደርሶበታል፡፡rnrnተከሳሹ በተጨማሪ 8 ሺህ 300 ዶላር የገንዘብ ቅጣት እና ሌላ የ18 ወር የገደብ የእስር ቅጣትም ተወስኖበታል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ






