Arts TVArts TV
← NewsLegal

ፍርድ ቤቱ አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን ጨምሮ በሌሎች ባለስልጣናት ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀን ፈቀደ

Arts TV · ኦክቶ 29 2018

ፍርድ ቤቱ አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን ጨምሮ በሌሎች ባለስልጣናት ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀን ፈቀደrnrnአርትስ 19/02/2011rnrnየፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን ጨምሮ የክልሉ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት፥ በተጠረጠሩበት የማፈናቀል፣ የአካል ጉዳትና ህይወትማለፍ ወንጀል ለፖሊስ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀን ፈቅዷል።rnrnአንደ ፋና ዘገባ መርማሪ ፖሊስ ቀሪ ስራዎችን ለማከናወን ተጨማሪ የ10 ቀን የጠየቀ ሲሆን፥ ተጠርጣሪዎቹ ተቃውሞ አቅርበዋል።rnrnተጠርጣሪዎቹ ፖሊስ በተደጋጋሚ ጊዜ ለተመሳሳይ ምርመራ በየጊዜው ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አግባብ አይደለም ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል።rnrnጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ለፖሊስ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀን በመፍቀድ ለጥቅምት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።rnrn 

More in Legal