Arts TVArts TV
← NewsLegal

የተለያዩ የጦር መሳሪያ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Arts TV · ዲሴም 28 2018

የተለያዩ የጦር መሳሪያ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ

rnአርትስ 19/04/2011rnrnበህገ-ወጥ መንገድ ወደ መሀል አገር ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ ጥይት መተማ ላይ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በፌደራል ፖሊስ መያዙን በጉምሩክ ኮሚሽን የባህርዳር ቅ/ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡rnrnግምታዊ ዋጋዉ 306 ሺ 640 ብር የሆነ 4ሺ492 የሽጉጥ እና 370 የብሬን ጥይት ትላንት ሳር በጫነ ካሮ (ጋሪ) ተደብቆ በመተማ በኩል ወደ መሀል አገር ሊገባ ሲል በፌደራል ፖሊስ በተደረገ የቁጥጥር ስራ የተያዘ ሲሆን በህገ ወጥ ስራው ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦችንም ይዞ ለፍርድ የማቅረብ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የቅ/ጽ/ቤቱ የጉምሩክ ህግ ተገዥነት ም/ስራ አስኪያጅ አቶ አላዩ ኩርፋ ገልጸዋል፡፡rnrnኮንትባንድ በፖለቲካዊ፤ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዘርፍ ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ቅ/ጽ/ቤቱ ኮንትሮባንድን ለመከላከል ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን ህብርተሰቡም ህገ-ወጦችን በመጠቆም እና በማጋለጡ በኩል እንደወትሮው ሁሉ ሊተባበር ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡rnrnምንጭ ገቢዎች ሚኒስቴር

More in Legal