የሥነ ምግባርና የጸረሙስና ኮሚሽን በሀገሪቱ የተካሄደዉ የተደራጀ ሌብነት ከአቅሜ በላይ ነበር አለ፡፡
rnአርትስ 19/04/2011rnrnበሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮችና ባለሀብቱ በቅንጅት ሲፈፀሙ የነበሩት የተደራጀ ሌብነት ከፌደራል ሥነ ምግባርና ከፀረሙስና ኮሚሽኑ አቅም በላይ እንደነበር ተገለፀ።rnrnየኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ አየልኝ ሙሉዓለም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት ሙስናና የተበላሹ አሠራሮች በሀገራችን በመጨመር ላይ ነው።rnrnየሙስና ብልሹ አሠራር በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተዋናይነት የተከወነ፣ የተደራጀ ሌብነት በመሆኑ ከሥነ ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽኑ አቅም በላይ ነበር ብለዋል።rnrnኮሚሽኑ ብቻውን የሚሠራው ነገር አለመኖሩን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ ሕብረተሰቡ፣ መገናኛ ብዙኃን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማትና መንግሥት በጋራ ሆነው በመሥራት አስተዋጽዖ ካላበረከቱ ኮሚሽኑ ብቻውን የሚወጣው አለመሆኑን ተናግረዋል።rnrnኮሚሽኑ በአዋጅ ሲቋቋም ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ከተገኝ የማጣራት የመመርመርና የመክሰስ መብት ነበረዉ፣ አሁን ግን ኮሚሽኑ የመጣለትን ጥቆማ በማጣራት ባገኝው መረጃ ተገቢውን ቅጣትና እርምጃ እንዲወሰድ ለሕግ አካል መረጃዎቹን የማቅረብ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነዉ ብለዋል።rn
rn