ካሜሮን የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ አሳስቦኛል አለችrn
rnrnአርትስ 26/02/2011rnrnበካሜሮን በርካታ የማእድን ማውጫ ስፍራወች እድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ህፃናት ከአቅማቸው በላይ በሆነ ስራ ተጠምደው ማየት ብዙም እንግዳ ነገር አይደለም፡፡rnrnይህን ደግሞ በማዕድን ቆፋሮ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰወች ሳይቀሩ በኩራት ይናገሩታል፡፡ ጀስቲን እምራማ የተባለ ግለሰብ እነዚህ ህፃናት የወርቅ ማእድን ፈልጎ በማውጣት ተካኑ ናቸው እኛም ብንሆን የተወሰነ ገንዘብ ስለምንሰጣቸው ተጠቃሚወች ናቸው ይላል፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ በዘገባው የካሜሮን ህፃናት በድህነት ተገፍተው ሳይወዱ በግዳቸው በነዚህ የማዕድን ቁፋሮ ቦታዎች ተበትነዋል ሲል አስነብቧል፡፡rnrnበተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህፃናት ጥበቃ ቢሮ በበኩሉ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ደጋግሞ ቢወተውትም እስካሁን ጠብ ያለ ውጤት አልተገኘም፡፡rnrnበድርጅቱ የህፃናት ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ባርባራ ጀማር እንደሚሉት በህፃናቱ ላይ እየደረሰ ያለውን ማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ቀውስ ለመቀየር የሁሉንም እገዛ ይፈልጋል፡፡rnrnየሀገሪቱ የሀይማኖት መሪዎች በበኩላቸው ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እንጂ ጉልበታቸው ወደሚበዘበዝበት ቦታ መሄድ የለባቸውም በማለት ድምፃቸውን ቢያሰሙም መልስ አላገኙም፡፡rnrnበዘቅተኛ ኑሮ የሚገኙት የህፃናቱ ወላጆችም ነገሩን እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ስለሚቆጥሩት ለልጆቻቸው ከመቆርቆር ይልቅ እንደ መልካም አጋጣሚ ይቆጥሩታል ነው የተባለው፡፡rnrn





