Arts TVArts TV
← NewsLegal

ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ የብረት ምርቶች ለህገ ወጥ ስራ እየዋሉ ነው ተባለ

Arts TV · ጃን 4 2019

ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ የብረት ምርቶች ለህገ ወጥ ስራ እየዋሉ ነው ተባለ
rnrn rnrnበኢንቨስትመንት ስም ከቀረጥ ነፃ ወደኢትዮጵያ የሚገቡ የብረት ምርቶች ለህገ ወጥ ስራ እየዋሉ በመሆኑ መንግስት ማግኘት የሚገባውን ከፍተኛ ገንዘብ እያሳጣው መሆኑን የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።rnrnየብረት ምርት ፍላጎት በከፍተኛ መጠን ባደገባት ኢትዮጵያ መንግስት ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት በሆቴሎች እና መሰል ዘርፎች ላይ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ብረት ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ፈቅዷል።rnrnነገር ግን ይህን የማበረታቻ እድል ባልተገባ ሁኔታ እየተጠቀሙ የሚገኙ ግለሰቦች መንግስትን ገንዘብ በማሳጣት ሀገሪቱን በከፍተኛ ደረጃ ሲጎዷት ቆይተዋል።rnrnየጉሙሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙለታ በየነ ከኤፍቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት በርካታ ድርጅቶች በሆቴል ዘርፍ ለመሰማራት ፍቃድ ቢያወጡም ማበረታቻውን ከተጠቀሙ በኋላ ግንባታውን  ማቋረጣቸውን ተናግረዋል።rnrnለአንድ ህንፃ ምን ያህል የብረት መጠን እንደሚያስፈልገው አለመታወቁ ይህንን ማጭበርበር  ለመከላከል አስቸጋሪ ሆኗል ብለዋል።rnrnጉሙሩክ ኮሚሽን ያቋቋመው የምርመራ ቡድን ኦዲት አድርጎ ሲጨርስ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምርም ተናግረዋል፡፡rnrn rn

rn

rn

More in Legal