አደጋ በደረሰበት የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ተገኘr

አርትስ 19/02/2011
rr
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በገንዳ ውሀ ከተማ አደጋ ደርሶበት በተገለበጠ የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ በርካታ የጦርመሳሪያ እና ገንዘብ መገኘቱን የመተማ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል ።
rተሽከርካሪው ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዝ የነበረ ሲሆን፥ በገንዳውሀ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ ኢንዱስትሪ መንደር በሚባል አካባቢ በትናትናው ዕለት ፍየል አድናለሁበሚል ምክንያት በመገልበጡ አደጋ ደርሷል ተብሏል።
rየከተማ አስተዳደሩና የወረዳው የጸጥታ ሀይሎች ባደረጉት ፍተሻ መሰረት 97 ክላሽን ኮፍ፣ 1 ሺህ 291 የቱርክ ሽጉጥ እና 3 ብሬን መገኘቱንም ነው ፅ/ቤቱ ጨምሮ ያስታወቀው ።
rn






