አንጎላ ሙስናን ለመዋጋት የተባበሩት መንግስታት ይርዳኝ እያለች ነውr
አርትስ 20/02.2018
rየሃገሪቱ ሃብት ተመዝብሮ በውጭ ሃገራት ተከማችቷል የሚሉት የአንጎላ ባለስልጣናት ሙስናን ለመዋጋት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲረዳቸው መማጸናቸውን አምነዋል።
rrጆርናል ዲ አንጎላ የተባለውን የአንጎላ ጋዜጣ ጠቅሶ ዘ ኢስት አፍሪካን እንደዘገበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዚህ ቀደም ድንበር ዘለል ሙስናን ለመከታተል የተቋቋመውን የሃገሪቱን ጠቅላይ ዐቃቢህግ ቢሮ ሲደግፍ ነበር።
rrአሁንም ተዘርፎ በውጭ ሃገር የተከማቸ ሃብቴን ለማስመለስ የድርጅቱ ድጋፍ ያስፈልገኛል እያለች ነው አንጎላ ።
rrየአንጎላ ብሄራዊ መጠባበቂያ ባንክ ገዢ የሆኑት ሚስተር ጆሴ ዴ ሊማ ማሳኖ እንዳረጋገጡት ከ30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚሆን የአንጎላ ሃብት በውጭ ሃገራት ተከማችቷል።
rrየውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማኑኤል አውግስቶ ደግሞ ባለፈው ወር ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው የተሰረቀውን የአንጎላን ሃብት ለማስመለስ ድጋፍ መጠየቃቸውንአረጋግጠዋል።





