አርትስ 10/03/2011rnrnተጠርጣሪው አቶ ገመቹ ጫላ በሚል ስም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻላ ቅርንጫፍ ባለፈው አርብ የባንክ ሂሳብ የከፈተ ነው።rnrnዛሬም ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በማምራት በተጭበረበረ የአምበሳ አውቶብስ ቼክ 14 ሚሊዮን 724 ሺህ ብር በማውጣት አርብ ዕለት ወደ ከፈተው የባንክ ሂሳብ ለማዛወር ሲል ነው በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ክትትል ተደርጎበትመያዙን ፋና የዘገበው ።rnrnተጠርጣሪው በሰዓቱ ለባንኩ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ኃላፊ 1 ሚሊዮን ብር ጉርሻ በማቅረብ እንዲፈፀምለት ለማግባባት ሞክሮም እንደነበር ተመልክቷል።





