አርትስ 28/02/2011
rrየኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው በትላንትናው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ ፤የክልሉ መንግስት ህዝቡን መሰረት አድርጎ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ እየሰራያለው ስራ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል።
rይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በተወሰኑ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን እና በአፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
rበተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻል ያለበት መሆኑን የክልሉ መንግስት ይገነዘባል ያሉት አቶ አድማሱ፥ በዚህ ላይም እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
rየክልሉ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ ትጥቅ መፍታት አለበት የሚል አቋም እንደሌለው እና ማንኛውንም አካል በመማረክ የማስተዳደር ፍላጎት እንደሌለውም ተናግረዋል።
rበአሁኑ ወቅትም የክልሉ መንግስት በኦሮሞ ስም ተደራጅተው ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመወያየት እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ አድማሱ፤ ወደ ፊትም ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።
rየኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ በጠብመንጃ ሳይሆን በውይይት፣ በመደማመጥና በመከባበር የሚፈታ መሆኑን በመግለጽ፥ የክልሉ መንግስትም የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ በመመለስ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚወያይ መሆኑንም አስታውቀዋል።
rአባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች አሁን እየመጣ ያለውን ለውጥ ጠብቀው በማስቀጠል የበኩላቸውን እንዲወጡም አቶ አድማሱ ጥሪ አቅርበዋል።





