Arts TVArts TV
← NewsLegal

በሙስና ወንጀል የሚፈለጉ ግለሰብን ሰነድ አሽሽተዋል የተባሉ ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረቡ

Arts TV · ኖቬም 23 2018

በሙስና ወንጀል የሚፈለጉ ግለሰብን ሰነድ አሽሽተዋል የተባሉ ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረቡ

rnአርትስ 14/03/2011rnrnበከባድ የሙስና ወንጀል ይፈለጉ የነበሩ የሜቴክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ብርጋዴር ጄነራል ሀድጉን ሰነዶች እንዲሸሹ አስደርገዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩት የሜቴክ የሰው ኃይል ልማት ኃላፊ የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል ሰጠኝ ካህሳይ ላይ ፖሊስ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠየቀ፡፡rnrnተጠርጣሪው ብርጋዴር ጄነራል ሀድጉ በሙስና ወንጀል እንደሚፈለጉ እያወቁ የተፈላጊው ጸሐፊም ከስራ ሰዓት ውጪ በቅዳሜ ዕለት ቢሮ ገብታ ሰነድ እንድታሸሽ በማድረጋቸው የሙስናን ወንጀል ምርመራን በማደናቀፍ ወንጀል ነው የተጠረጠሩት፡፡rnrnተጠርጣሪው ቀደም ባለው ጊዜ አቅም ስለሌለኝ መንግስት ተከላካይ ጠበቃ ይመደብልኝ በማለት ያገኙትን ይሁንታ ተከትሎ ፖሊስ ከቀጠሮው በፊት በነበሩት ጥቂት ቀናት ተጠርጣሪው ሃብት እንዳላቸው አጣርቻለሁ ብሏል፡፡rnrnተጠርጣሪው በ5 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች 250 ሺህ ብር ተቀማጭ እንዳላቸዉ የገለፀው ፖሊስ አቅም እያላቸው የለኝም በማለት ፍርድ ቤቱን አሳስተዋል ብሏል፡፡rnrnተጠርጣሪው በበኩላቸው ሂሳቦቹ የታገዱ ናቸው፤ ችሎቱም የባንክ ሂሳቦቹን ይመርምርልኝ፤ ከዚህ አንጻር በመንግስት ጠበቃ የመወከል መብቴን ላጣ አይገባም ብለዋል።rnrnኢቢሲ እንደዘገበዉ ችሎቱም አሁን ያለው ሂሳባቸው ተጣርቶ እንዲቀርብና ተጨማሪ ማስረጃ ፖሊስ ሰብስቦ በሰባት ቀን አንዲያቀርብ በማዘዝ ለህዳር 20 ቀን 2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

More in Legal