ለስድስት ወራት በቆየው የምህረት አዋጅ ከ13 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለፀ።rnrnሀምሌ 13 2010 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ስራ የገባው የምህረት አዋጅ ከትናንት በስቲያ ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም ተጠናቅቋል።rnrnየምህረት አዋጁ ተፈፃሚ ሆኖ በቆየባቸው የስድስት ወራት ጊዜያትም ከ13 ሺህ 200 በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።rnrnአዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከተጠናቀቀበት ዕለት ድረስ የወንጀል ክሳቸው በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተይዞ የነበሩት እነዚሁ ግለሰቦች የምህረት ሰርተፊኬት መውሰዳቸውንም ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።rnrnአዋጁ ስራ ላይ የዋለው ከግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ.ም በፊት በተፈፀሙ ወንጀሎች ይመለከታቸዋል ለተባሉ ግለሰቦች ምህረት ለማድረግ እንደነበር ዐቃቢ ሀግ አስታውሷል።rnrnበዚህም መሰረት ክትትል የሚደረግባቸው፣ ምርመራ የተጀመረባቸው እና ውሳኔ አግኝተው በየማረሚያ ቤቱ የሚገኙ ግለሰቦች የአዋጁ ተጠቃሚ ሆነዋል።rnrnከምህረት አዋጁ ተጠቃሚዎች ውስጥም አብዛኞቹ በአካል በመቅረብ የምህረት ሰርተፊኬት የወሰዱ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ደግሞ በተወካይ እና በድረ-ገፅ አማካኝነት ፎርም ሞልተው መውሰዳቸው ተገልጿል።rnrn