<strong>32ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የካቲት 11 እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡</strong>rnrnየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ከየካቲት 7 እስከ 8 የሚኒስትሮች ስብሰባ የሚካሄድ መሆኑን ገልፀው ከየካቲት 10 እስከ 11 ድረስ ደግሞ የመሪዎቹ ስብሰባ ይቀጥላል ብለዋል፡፡rnrnበ32ኛው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወቅት የአፍሪካ ህብረት ተቋማዊ ሪፎርምን በተመለከተ በጥልቀት ውይይት የሚደረግበት እና የወቅቱ የህብረቱ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜን ጨምሮ ዋና ፀሃፊው ሙሳ ፋቂ መሀመት የአፈፃፀም ሪፖርታቸውን የሚያቀርቡበት ነው ተብሏል።rnrnበጉባኤው ላይ ከሌሎች ጊዜያቶች በተለየ የአፍሪካ እና የኢትዮጵያ አርቲስቶች አፍሪካን በሚያጎላ መልኩ ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡበት እና አፍሪካዊ ትዕይንቶች የሚቀርቡበት እንዲሆን ቅድመ ዝግጅት መደረጉንም ሀላፊው ተናግረዋል፡፡rnrn rnrn rnrn





