አልበሽር ለሰልፍ በወጡ ተቃዋሚዎች ግድያ ተከሰሱ፡፡rnrnቢቢሲ እንደዘገበዉ ክሱ የእርሳቸውን አስተዳደር በመቃወም አደባባይ በመውጣት ህይዎታቸው ባለፉ ዜጎች ምክንያት ነዉ፡፡rnrnኦማር ሃሰን አልበሽር ሱዳንን ለ30 አመታት ያክል የመሩ ሲሆንrnrnባለፈው ሚያዚያ ወር ም በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን መዉረዳቸዉ ይታወሳል፡፡rnrnአሁን ላይ በማረሚያ ቤት የሚገኙት አልበሽር ከህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ በሚል ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየተጣራም ይገኛል፡፡rnrnአልበሽር ቤተሰቦቻቸው በህገ ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ በመጠቀም ወንጀል የተመሰረተባቸውን ክስ እንዲከራከሩላቸው አራት ጠበቆችን ቀጥረውላቸዉ ነበር ፡፡






