Arts TVArts TV
← NewsHealth

1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በአይነቱ ልዩ የሆነ የህፃናት ሆስፒታል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው

Arts TV · ኤፕሪ 11 2019

1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በአይነቱ ልዩ የሆነ የህፃናት ሆስፒታል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው

1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በአይነቱ ልዩ የሆነ የህፃናት ሆስፒታል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነውrnrnየኢትዮጵያ መንግስት ከኔዘርላንድ መንግስት ጋር በመተባበር በ877 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ በአለርቲ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ በአይነቱ ልዩ እና የመጀመሪያ የሆነ አዲስ የህፃናት አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡rnrnየኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት በህፃናት ዙሪያ የሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶችን ማሻሻልና ማዘመን አስፈላጊ ከመሆኑ አንጻር ሆስፒታሉ በህፃናት ዙሪያ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ የልብ፣ነርቭ፣የኩላሊት እንዲሁም ከ30 በላይ የሚደርሱ የህክምና ስፔሻሊቲ አገልግሎት እንደሚኖሩት ተናግረዋል፡፡rnrnበአለርት ሆስፒታል ውስጥ የሚገነባው የህፃናት አጠቃላይ ሆስፒታል በሁለት አመት እንደሚጠናቀቅና 317 አልጋዎች እንደሚኖሩት ወጪውም በኔዘርላንድ መንግስት፣በአሜርካን ፋውንደሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሸፍን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

More in Health