Arts TVArts TV
← NewsAfrica

ፊሊክስ ሽሴኪዲ በነገው እለት የኮንጎ ፕሬዝዳንት ለመሆን ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ፡፡

Arts TV · ጃን 20 2019

ፊሊክስ ሽሴኪዲ በነገው እለት የኮንጎ ፕሬዝዳንት ለመሆን ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ፡፡rnrnየሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት በውዝግብ በተሞላው የዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ የምርጫ ውጤት የመጨረሻ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡rnrnምርጫው  እንደተጠናቀቀ ሺሴኪዲ ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚሺኑ ይፋ ሲያደርግ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ታዛቢዎቸ  ያቀረቡልኝ ሪፖርት እና ውጤቱ ተለያልቷ በሚል ተቃውሞዋን አሰምታለች፡፡rnrnየአፍሪካ ህብረትም ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ በጉዳዩ ዙሪያ መክሮ የምርጫው ጠቅላላ ውጤት ዘግይቶ እንዲገለፅ የሚል ምከረ ሃሳብ አቅርቦ ነበር፡፡rnrnይሁን እንጂ የኮንጎ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ሺሴኪዲ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ማገልገል የሚያስችላቸውን ድምፅ አግኝተዋል በማለት ወስኗል፡፡rnrnአሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ፊሊክስ ሺሴኪዲ ኮንጎ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1960 ነፃነቷን ካገኘች ወዲህ  በምርጫ ወደ ስለጣን የመጡ የመጀመሪያው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ናቸው፡፡rnrnበሀሪቱ በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር ሲደረግም ይህ በኮንጎ ታሪክ የመጀመሪያው ነው፡፡rnrnአዲሱ ፕሬዝዳንት የምርጫ ኮሚሺኑ ባስቀመጠው መርሀ ግብር መሰረት በነገው እለት ቃለ መሃላ ፈፅመው ስልጣናቸውን ከጆሴፍ ካቢል ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

More in Africa