Arts TVArts TV
← NewsAfrica

ግብጽ በ2022 የኤሌክትሪክ ድጎማ ልታቋርጥ መሆኑን ገለጸች ፡፡

Arts TV · ማርች 29 2019

ግብጽ በ2022 የኤሌክትሪክ ድጎማ ልታቋርጥ መሆኑን ገለጸች ፡፡

ግብጽ በ2022 የኤሌክትሪክ ድጎማ ልታቋርጥ መሆኑን ገለጸች ፡፡rnrnግብጽ በኤሌክትሪክ ላይ የምታደርገውን ድጎማ በፈረንጆቹ 2022 ሙሉ ለሙሉ ልታቆም መሆኗን ያስታወቁት የሀገሪቱ ኤሌክረትሪክ ሚኒስትር መሐመድ ሻከር፤ ሀገሪቱ  የምትተገብረው  የኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድ አንዱ አካል ነው ብለዋል፡፡rnrnሚኒስትሩ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው  በሰጡት መግለጫ የኤሌክትሪክ ክፍያ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት እየጨመረ ይሄዳል ያሉ ሲሆን ፤ድጎማውን ማቋረጥ ያስፈለገው የመጠጥ ውሃ፣የኤልክትሪክና የጽዳት አገልግሎቶችን  ለህዝብ የሚሰጡ ተቋማትን  ወደ ግል የማዘዋወር እቅድ በመኖሩ ነው ብለዋል፡፡rnrnበተመሳሳይም መንግስት ለቤት ውስጥ መጠቀሚያ ነዳጅ፣ቤንዚል እና ናፍጣ ላይ ሲያደርግ የቆየውን ድጎማ እንደሚያቆም አስታውቋል፡፡rnrnበውሳኔው የተነሳ በከፋ ድህነት የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግብጻዊያን መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት የሚችሉበት ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ ተብሏል፡፡rnrnእንደ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ ላለፉት አራት አመታት ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ ወደስልጣን  ከመጡ ወዲህ የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ፍጆታዋ እየጨመረ መምጣቱ ተነግሯል፡፡rnrnእንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ ዋጋው መውረድ ተከትሎ የተከሰተውን የዋጋ ግሽበት ለማካካስ በ2022 የሀገሪቱን የግብር ክፍያ መጠን በ131 በመቶ ላማሳደግም ታቅዷል፡፡rnrnይሄን የአልሲሲን ውሳኔ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ግብጻዊያን ተቃሙሟቸውን እየገለጹ ሲሆን ፕሬዜዳንቱ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸው ይልቀቁ የሚሉ ድምጾች በርክተዋል ነው የተባለው፡፡rnrn 

More in Africa