Arts TVArts TV
← NewsAfrica

የፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ዙፋን አሁንም እየተነቃነቀ ነው

Arts TV · ጃን 25 2019

<strong>የፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ዙፋን አሁንም እየተነቃነቀ ነው፡፡</strong>rnrnበሱዳን በወባ ሳቢያ የተቀሰቀሰው ቁጣ መልኩን ቀይሮ የአስተዳደር ለውጥ  አጀንዳ ከሆነ ከወር በላይ አስቆጥሯል፡፡rnrnለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ የሚወጡ ሰዎች እና የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ በመግባታቸው እስካሁን የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 29 ከፍ ማለቱም ተሰምቷል፡፡rnrnነገር ግን ይህን ያሉት በመንግስት በኩል ተወክለው ነገሩን አጣራን ያሉት አካላት ናቸው እንጂ ገለልተኛ ነን የሚሉ ወገኖች ቁጥሩን ወደ 40 ያስጠጉታል፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት አልበሽር ሰሞኑን ወደ ኳታር ተጉዘው ባቀረቡት ጥያቄ ከዶሀ መንግስት ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል፡፡rnrnይሁን እንጂ አሁን በካርቱም እና በበርካታ የሱዳን ከተሞች እየተባባሰ የመጣው አመፅ መልኩን ቀይሮ አልበሽር ከስልጣናቸው ይውረዱ የሚል በመሆኑ ከዚህ በኋላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ቢደረግም የረፈደበት መፍትሄ ነው ተብሏል፡፡rnrnአልበሽር እና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ስልጣን ማስተላለፍ የሚቻለው በምርጫ ብቻ ነው  ከዚህ ውጭ የሚደረግ እንቅስቃሴ ሁሉ ህገ ወጥ ነው ቢሉም ሰሚ ጆሮ ግን አላገኙም፡፡rnrn&nbsp;

More in Africa