Arts TVArts TV
← NewsHealth

የጤና ሚኒስቴር ለተፈናቃዮች በጤና ባለሙያዎች የሚደረገው ድጋፍና ተጠናክሮ  ቀጥሏል አለ፡፡

Arts TV · ኤፕሪ 4 2019

የጤና ሚኒስቴር ለተፈናቃዮች በጤና ባለሙያዎች የሚደረገው ድጋፍና ተጠናክሮ  ቀጥሏል አለ፡፡

የጤና ሚኒስቴር ለተፈናቃዮች በጤና ባለሙያዎች የሚደረገው ድጋፍና ተጠናክሮ  ቀጥሏል አለ፡፡rnrnየጤና ሚኒስቴር በጌዲዮ ዞን ተፈናቃዮች ድጋፍ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች፡ የተለያዩ መድሃኒቶች እና ሌሎች ግበአቶችን ወደ ስፍራው ከመላክ በተጨማሪ በጤና ባለሙያዎች የሚደረጉ የተለያዩ የህክምና ድጋፍና ክትትል ስራዎች መቀጠላቸውን ሚኒስቴሩ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡rnrnቁጥራቸው 22 ሺህ 895 የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ከምግብ ዕጥረት ጋር ተያይዞ የገጠሟቸውን የጤና እክሎች በምርመራ በመለየት ተገቢውን ምርመራና ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡rnrnእንዲሁም በተፈናቃዮቹ የተለያዩ መጠለያዎች በተደረጉ ምርመራዎች የተለያዩ የጤና እክል ያጋጠማቸው 29,823 ሰዎች ተለይተው ህክምና እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡rnrnከአሁን ቀደም ወደ ስፍራው ካቀኑት ባለሙያዎች በተጨማሪ ባሳለፍነው ሳምንት 11 የአዕምሮ ጤና ባለሙያዎችም ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግር የተጋለጡ ሰዎች የድጋፍና ክትትል ስራ እንዲያከናውኑ የተሰማሩ መሆኑንም ሰምተናል፡፡rnrnከአሁን በፊት 15 ሀኪሞች፣ 36 ነርሶች፣ 5 የአካባቢ ጤና ባለሙያዎች እና 5 የኢፒዲሞሎጂ ባለሙያዎች እንዲሁም ከ121 በላይ የጤና ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ማቅናታቸውንና የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ቅኝቶችና ዳሰሳዎችን ከማድረግ በተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን በመግለጫዉ ተጠቅሷል፡፡

More in Health