የኢትዮጵያ ክህምና ማህበር ለሕክምና ባለሙያዎች ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በሚበልጥ ወጪ መንደር ልገነባ ነው አለ
rnአርትስ 25/03/2011rnየኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር በ2.4 ቢሊዮን ዶላር ለ7 ሺህ የሕክምና ባለሙያዎች ቤት፣ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል፣ ሪዞርትና መናፈሻ ያካተተ መንደር በአዲስ አበባ እንደሚገነባ አስታውቋል፡፡rnrnየማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ገሚቺስ ማሞ እንደገለጹት፣ የግንባታው ሥራ የሚከናወነው በሁለት ዕርከን ሲሆን፣ በመጀመርያው ዕርከን የሚከናወነው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ነው፡፡rnrnየቤቶቹ ግንባታ ከተጠናቀቀ በኃላ በሁለተኛ ዕርከን የሆቴል፣ የሪዞርትና የመናፈሻ ግንባታ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡rnrnየመኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ ለ30 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና ግንባታውም በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ዶ/ር ገመቺስ ተናግረዋል፡፡rnrnግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላም ለሕክምና ባለሙያዎች የሚከፋፈለው በግዥ ነው፣ ግዥውም የሚፈጸመው በረዥም ጊዜ በሚከፈል ብድር መሆኑ ተነግሯል፡፡rnrnየአዲስ አበባው የመንደር ግንባታ ከተጠናቀቀ በኋላ በእያንዳንዱ ክልል ርዕስ ከተማ ቢያንስ ለ500 የሕክምና ባለሙያዎች የሚውል መኖሪያ ቤት የመገንባት ዕቅድ መኖሩንም ዶ/ር ገመቺስ ተናግረዋል፡፡