Arts TVArts TV
← NewsHealth

የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት (ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ድንጋጌ ከግንቦት 21 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

Arts TV · ኤፕሪ 10 2019

የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት (ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ድንጋጌ ከግንቦት 21 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡rnrnየአልኮል መጠጥ በብሮድካስት (ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ድንጋጌ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112 በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ የካቲት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ታትሞ ወጥቶ ነበርrnrnበአዋጁ አንቀጽ 74(4) መሰረት የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት (ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ድንጋጌ ከግንቦት 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡rnrnበዚሁ መሰረት ማንኛውም የአልኮል መጠጥ የማስታወቂያ አስነጋሪ እና የብሮድካስት ሚድያ ለህጉ ተፈጻሚነት ተገቢውን ዝግጅት እንድያደርጉ እና ለህጉ መፈጸም የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ጤና ሚኒስቴር ጠይቋል፡፡

More in Health