<strong>የቱኒዚያ መንግስት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰራተኞቹ ጋር ተኳርፏል</strong>rnrnበቱኒዚያ በተፅእኖ ፈጣሪነቱ የሚታወቀው ጀኔራል ሌበር ዩኒየን በመላ ሀገሪቱ መንግስትን ለመቃወም ባደረገው ጥሪ የአውቶቡስ፣ የባቡር እና የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል፡፡rnrnበሀገሪቱ መንግስት የሚተዳደረው ቱኒዚያ ኤየር የተባለው አየር መንገድ ነገሩ ሳይለይለት በረራ አላደርግም ብሎ ደንበኞቹ የጉዞ ፕሮግራማቸውን ለሌላ ቀን እንዲያዛውሩ በመንገር አሰናብቷቸዋል፡፡rnrnትምህርት ቤቶች ፣ሆስፒታሎች እና ሌሎች የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማትም በአመፁ ሳቢያ ተዘግተው ውለዋል ነው የተባለው፡፡rnrnየሰራተኛ ማህበሩ የተቃውሞ ሰልፉን የጠራው መንግስት ለ670 ሺህ ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ባለመመለሱ ነው፡፡rnrnሮይተርስ እንደዘገበው የአሁኑ አመፅ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2013 አንድ የተቃዋሚ ፖለቲከኛ መገደላቸውን ተከትሎ ከተደረገው ሰልፍ ወዲህ በትልቅነቱ ተወዳዳሪ የለውም፡፡rnrnየቱኒዚያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዩሱፍ ቻህድ አመፁ ብዙ ዋጋ ቢያስከፍለንም ሀገራችን የገባችበት የኢኮኖሚ ቀውስ በተጠየቀው ልክ ደሞዝ ለመጨመር አያስችላትም ነው ያሉት፡፡rnrnየሰራተኛ ማህበሩ የጠየቀው የደሞዝ ጭማሪ መንግስትን 850 ሚሊዮን ዶላር የሚያስወጣው ሲሆን ለመክፈል የተስማማው ግን ከግማሽ በታች ነው፡፡rnrnቱኒዚያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ በፈረንረጆቹ 2016 ለተፈቀደላት የ2.8 ቢሊዮን ዶላር ብድር የተቀመጠላትን ቅድመ ሁኔታ ለማሟላት እየታገለች ትገኛለች፡፡rnrn






