የህብረተሰብን ጤና ለመጠበቅ ሁነኛ መፍትሄ ነው የተባለው የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀረበ።
rnአርትስ 03/04/11rnrnየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክር ቤቱ ላለፉት ስምንት ዓመታት ሲሰራበት የቆየውን የምግብና መድሃኒት አስተዳደር አዋጅ የሚተካውን ይህንን አዲስ ረቂቅ በማየት ለሚመለከተው አካል መርቶታል።rnrnጤንነቱ ባልተጠበቀ ምግብና መድሃኒት ምክንያት የህብረተሰቡ ጤና አደጋ ላይ እንዳይወቅድ መከላከል የአዲሱ አዋጅ ቁልፍ ዓላማ ነው ብለዋል የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ጫላ ለሚ ።rnrnአቶ ጫላ የረቂቁን ማብራሪያ ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት ይህ አዋጅ ደህንነቱና ውጤታማነቱ ባልተረጋገጠ የህክምና መሳሪያ ሳቢያ የሰው ህይወት ላይ የሚደርሰውን የጤና ችግር ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይረዳል ።rnrnነባሩን አዋጅ መቀየር ያስፈለገው የቁጥጥር ስራውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስና በመስኩ ያለው የቴክሎጂ አጠቃቀም ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር ነው ተብሏል በማብራሪያው ። ዘገባው የኢዜአ ነው።