ኬንያ የዋና አየር መንገዷን ተርሚናል ለጊዜው ዘግታለች፡፡rnrnናይሮቢ በሚገኘው ጆሞ ኬንያታ አየር መንገድ ተርሚናል በእቃ ማስተላለፊያው ክፍል የተነሳ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ነው ኬንያ ይህን እርምጃ እንድትወስድ ያስገደዳት፡፡rnrnየኬንያ አየር መንገድ ባለ ስልጣናት እንደተናገሩት ተርሚናሉ አገልግሎቱን እንዲያቆም የተደረገው መንገደኞች አደጋ እንዳይደርስባቸው ከአካባቢው ለማሸሽ ነው፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በአየር መንገዱ የእሳት ቢነሳም በመንገደኞችንም ሆነ በሰራተኞች ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም፡፡rnrnየጆሞ ኬንያታ አየር መንገድ የኢትዮጰያ አየር መንገድን ጨምሮ የቱርክ፣ የእንግሊዝ እና የኤሜሬትስ አየር መንገዶችን በማስተናግድ ይታወቃል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ






