ኬንያ ዓለም አቀፍ የመምህራን ሽልማት በማሸነፍ በአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር ሆነች፡፡rnrnኬንያ ይህን የክብር ሽልማት ያሸነፈችው በ36 ዓመቱ የሳይንስ መምህር ፒተር ታቢቺ አማካይነት ነው፡፡rnrnታቢቺ በስልጣኔ ወደፊት ለመጓዝ ሳይንስ ሁነኛው መንገድ ነው የሚል ፅኑ አቋም ይዞ ተማሪዎቹን በራሱ ወጭ ሲያግዝ እንደነበር በመድረኩ ተመስክሮለታል፡፡rnrnየሂሳብ እና የፊዚክስ ትምህርቶችን አጣምሮ የሚያስተምረው ታቢቺ ድሀ ተማሪዎችን ለመርዳት ሲል 80 በመቶ የሚሆነውን የወር ደመወዙን ፍላጎታቸውን ለማሟላት ያውል እንደነበርም ተነግሯል፡፡rnrnበተለይ ተሰጥኦን ማዳበር የሚያስችል “ታለንት ነርቸሪንግ” የተባለ ክለብ አቋቁሞ በሳይን ምህርት ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች በመለየት "ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ያደረገው ጥረት መልካም ፍሬ አፍርቶለታል፡፡rnrnበዚህ ክለብ ውስጥ ችሎታቸውን ሲያጎለብቱ ከነበሩት የታቢቺ ተማሪዎች መካከልም 60 በመቶ የሚሆኑት ለሀገር አቀፍ ውድድር ብቁ ሆነው ተገኝተዋል፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ታቢቺ ሽልማቱ የእኔ ሳይሆን የኬንያ ታዳጊዎች እና ወጣቶች የስራ ውጤት ስለሆነ ሀገራቸውን በማስጠራታቸው ሊኮሩ ይገባል ብሏል፡፡rnrnመምህሩን 58 ተማሪዎች በአንድ ክፍል አንዲት ኮምፒዩተር ተጋርተው የሚማሩበት ሁኔታ ተስፋ ሳያስቆርጠው ነገሮችን ለመቀየር የተጓዘው ርቀት ነው ለዚህ ሽልማት ያበቃው፡፡rnrnይህ ኬንያን ብሎም አፍሪካን ያስጠራ ታታሪ መምህር ቫርኪ ፋውንዴሽ በተባለ ተቋም በተሰጠው እውቅና የአንድ ሚሊዮን ደላር ተሸላሚ ሲሆን የተቋሙ ዓለም አቀፍ አምሳደር ሆኖም ያገለግላል፡፡rnrnታቢቺ ከ179 ሀገራት ለውድድሩ ከተመዘገቡ 10 ሺህ እጩዎች መካከል ነው የሱ ስራ ጎልቶ በመውጣቱ ሽልማቱን ያሸነፈው፡፡ ይሄም በአፍሪካ ታሪክ ኬንያን የመጀመሪያዋ አድርጓታል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ






