<strong>ከአፍሪካ ህብረት መስራች መሪዎች አንዱ የሆኑት የቀድሞ የኢትዮጵያ ንጉሰ ቀዳማዊ </strong><strong>ሃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ሀውልት ተገነባላቸው</strong> ።rnrnሀውልቱ በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ቅጥር ግቢ ውስጥ የቆመ ሲሆን የሃውልቱ ዲዛይን እና ግንባታ የተከናወነውም በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አለ ፈለገ ሰላም የስነ-ጥበብ ትምህርት ቤት መሆኑ ተነግሯል፡፡rnrnየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አቶ ነብያት ጌታቸው እንዳሉት ሃውልቱ የተገነባው እ.ኢ.አ በ 2017 የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ወቅት ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ለአፍሪካ ፀረ- ቅኝ ግዛት ትግል ያደረጉትን አስተዋፆ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሀውልት እንዲቆምላቸው በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ነው።
← NewsAfrica
ከአፍሪካ ህብረት መስራች መሪዎች አንዱ የሆኑት የቀድሞ የኢትዮጵያ ንጉሰ ቀዳማዊ ሃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ሀውልት ተገነባላቸው
Arts TV · ፌብ 1 2019





