አፍሪካን አርቲስት ፒስ ኢኒሼቲቭ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይንና ፕሬዝዳንት ኢሳያስን ልሸልም ነዉ አለ፡፡rnrnአፍሪካን አርቲስት ፒስ ኢኒሼቲቭ የተሰኘ በአፍሪካ ህብረት ስር ያለ አንድ የሽልማት ድርጅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ልሸልም ነው አለ፡፡rnrnተቋሙ መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ሰላም እንዲሰፍን እና የህዝብለህዝብ ትስስሩ ዳግም እንዲመለስ ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት ሲል የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 30/2011 ዓ.ም ሽልማቱን እንደሚያበረክት በኢትዮጵያ የአፍሪካን አርቲስት ፒስ ኢኒሼቲቭ አስተባባሪ አቶ አብይ ሽመልስ ገልፀዋል፡፡rnrnከ5 አመታት በፊት በ28ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የተቋቋመው እንቅስቃሴው በአህጉር ደረጃ አርቲስቶች እና ኪነጥበብ ላይ ያሉ ባለሞያዎችን በማስተባበር ለሰላም መስፈን የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የሚያስተባብር እንቅስቃሴ እንደሆነም ሰምተናል፡፡rnrnበመሆኑም የእውቅና ሽልምቱን ላለፉት አራት አመታት በአህጉሪቱ ለሰላም እና መረጋጋት የሚበረታታ ስራ ለሰሩ አካላት ሲሰጥ መቆየቱን ተቋሙ አስታውቋል፡፡rnrnለዋቢነትም በአፍሪካ ሀብረት ለሴቶች ሰላም እና መረጋጋት ላይ አስተዋፅኦ ያደረጉትን ማደም ቤኒታዲዮችን መሸለሙ ይታወሳል፡፡
← NewsAfrica
አፍሪካን አርቲስት ፒስ ኢኒሼቲቭ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይንና ፕሬዝዳንት ኢሳያስን ልሸልም ነዉ አለ፡፡
Arts TV · ማርች 4 2019





