Arts TVArts TV
← NewsHealth

አለም አቀፍ የካንሰር ቀን በሀገራችን ለ12ኛ ጊዜ ተከበረ

Arts TV · ፌብ 4 2019

አለም አቀፍ የካንሰር ቀን በሀገራችን ለ12ኛ ጊዜ ተከበረ

አለም አቀፍ የካንሰር ቀን በሀገራችን ለ12ኛ ጊዜ ተከበረrnrnየዘንድሮው አለም አቀፍ የካንሰር ቀን ‹‹እራሴን እና ቤተሰቤን ከካንሰር ለመከላከል ቆርጫለሁ›› በሚል መሪቃል ነው ተከብሮ የዋለው፡፡rnrnበጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የካንሰር አማካሪ ዶክተር ኩኑዝ አቡበከር ለአርትስ እንደተናገሩት ቀኑን አስቦ መዋል ያስፈለገው ማህበረሰቡ ውስጥ ካንሰር የማይድን በሽታ ነው ለሚለው አመለካከት ግንዛቤን ለመፍጠር ነው፡፡rnrnእንደ ዶክተር ኩኑዝ ገለፃ ካንሰር በጊዜ ከተደረሰበት መከላከል እና ማዳን የሚቻል ህመም ነው፡፡rnrnበኢትዮጵያ በየአመቱ ከ65ሺህ በላይ አዳዲስ የካንሰር ህሙማን የሚመዘገቡ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 30 በመቶ የሚሆኑት የጡት ካንሰር የተያዙ ሰዎች ናቸው፡፡rnrnየመሃጸን በር እና የአንጀት ካንሰር ደግሞ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በሀገራችን በብዛት የሚስተዋሉት የካንሰር አይነቶች ናቸው፡፡rnrnከካንሰር ህክምና ጋር ተያይዞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በገፃቸው እንዳሰፈሩት ሰባት የጨረር ህክምና መሳሪያ (LINAC Machine) በ26.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ግዥ ተፈፅሞ ሶስቱ በተከላ ላይ ሲሆን አራቱ ደግሞ የማዕከሉ ግንባታ እስኪጠናቀቅ እየጠበቁ ይገኛል ፡፡rnከሀገራችን የካንሰር ህመም አይነት ጋር ጥናት ተደርጎ 51 አይነት የኬሞቴራፒ መድኀኒቶች ግዥ ተፈፅሞ ከመድኀኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ቀጥታ ወደ ካንሰር ማእከላት የሚሄድበት አሰራርም መዘርጋቱን ሚኒስትሩ በገፃቸው አስፍረዋል፡፡

More in Health