ባህላዊ ህክምናን ጨምሮ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ና ስነ ምግባር ላይ የሚያተኩረዉ አራተኛው አመታዊ የጤና ሳይንስ ጉባኤ እየተካሄደ ነዉ፡፡rnለአራት ቀን በሚካሄደዉ ጉባኤ የጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ፤ በጤና ፖሊሲ ክለሳ፤ ተላላፊ በሽታዎች፤የላብራቶሪ አገልግሎት እና ድንገተኛ ህክምና አሰጣጥን አስመልክቶ ለሚሻሻሉ ስራዎች መነሻ ሀሳብ ያሳያል፡፡rnrnአራተኛውን የጤና ሳይንስ ጉባኤን በንግግር የከፈቱት የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በዚህ የጥራትና የምርምር ጉባኤ የሚነሱ ውጤቶች በቀጣይ በጤናው ዘርፍ ለሚደረጉ ለውጦች አጋዥ ይሆናሉ ብለዋል፡፡rnrnበተለይም ደግሞ አመታዊ የጤና ሳይንስ ጉባኤ በአራት ቀን ቆይታው የመረጃ አብዩት፤ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፤ የስነ ምግባር፤ የድንገተኛ አደጋዎች ላብራቶሪና ባህላዊ ህክምና ላይ ትኩረት ተሰጥቶበት የጥናታዊ ስራዎች ይቀርባሉ፡፡rnrnበዚህ ጉባዔ ላይ ከ500 በላይ ተመራማሪዎች፥ ተማሪዎች እና ባለድርሻ አካላት የተገኙበት ሲሆን ከ200 በላይ ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ገልጸዋል: :rnrnበተያያዘምrnrnበተጨማርም ከሰኞ ሚያዚያ 28 /2011 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሲጋራ የማይጨስበት ተቋም መሆኑን አውጇል::rnrnጉባኤውን አስመልክቶ የተዘጋጀ ኢግዝቢሽን በጉባኤተኞቹ የተጎበኘ ሲሆን የኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ድኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ና በኢትዮጵያ የ CDC country Director ዶ/ር ክርስቲን ሮዝ በጉባኤው ላይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል: :
← NewsHealth
ባህላዊ ህክምናን ጨምሮ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ና ስነ ምግባር ላይ የሚያተኩረዉ አራተኛው አመታዊ የጤና ሳይንስ ጉባኤ እየተካሄደ ነዉ፡፡
Arts TV · ሜይ 7 2019






