Arts TVArts TV
← NewsHealth

በ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጭ የተገነባው ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች ማስወገጃ ማዕከል ስራ ሊጀምር ነው

Arts TV · ዲሴም 4 2018

በ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጭ የተገነባው ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች ማስወገጃ ማዕከል ስራ ሊጀምር ነው

rnአርትስ 25/03/2011rnrnበ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጭ የተገነባው የአዳማ ከተማ ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶች ማቃጠያ ዘመናዊ ማዕከል ከ 2 ሳምንት በኋላ ስራ አንደሚጀምር የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።rnrnየጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ማዕከሉን ጎብኝተዋል፡፡rnrnማዕከሉ ጊዜያቸው ካለፈባቸው መድሀኒቶች አወጋገድ ጋር ተያይዞ ከህብረተሰቡ የሚነሳውን ቅሬታ እንደሚፈታ ተነግሯል፡፡rnrnጊዜያቸው ያለፋባቸው መድሃኒቶችን በማስወገድ አቅም  በአፍሪካ የመጀመሪያው  እንደሆነ የተነገረለት ማዕከሉ  በሰዓት 1 ሺ ኪሎ ግራም ጊዜ ያለፈባቸውን መድሀኒቶች ማቃጠል የሚችል ነው ተብሏል።rnrnበሌሎች 7 ቦታዎች ተመሳሳይ ማዕከላት እየተገነቡ ሲሆን፥ ከ 3 ወር በኋላ ወደ ስራ እንደሚገቡም ታውቋል።rnrnእንደ ጤናጥበቃ ሚኒስቴር  መረጃ ይህን ማዕከል ጨምሮ በግንባታ ላይ ለሚገኙት ማዕከላት ከ 13 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጭ ተደርጓል፡፡

More in Health