በደቡብ አፍሪካ በጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ50 በላይ ደርሷል፡፡rnrnኩዋዙሉ ናታን በተባለው የሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኝ አካባቢ የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ መነዋሪዎች ላይትልቅ ጉዳት አድርሷል፡፡rnrnአልጀዚራ እንደዘገበው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቤቶች ፍርስራሾች ውስጥ የተቀበሩ ሰዎችን የማፈላለጉን ስራ እንደቀጠሉ ናቸው፡፡rnrnበወደብ ከተማዋ ደርባን በርካታ ህንፃዎች እና መንገዶች በአደጋው ሳቢያ የፈራረሱ ሲሆን ኬፕ ታወን አካባቢ ሶስት ሰዎች መሞታቸውም ተሰምቷል፡፡rnrnየሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አደጋው የደረሰበትን አካባቢ ከገጎበኙ በኋላ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሰዎችን ለማዳን ለሚያደርጉት ጥረት ምስጋና አውርበዋል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ






