Arts TVArts TV
← NewsAfrica

በደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት በደረሰው የጎርፍ አደጋ ለተጎጅዎች የሚሆን የውጭ እርዳታ መግባት ጀምሯል፡፡

Arts TV · ማርች 21 2019

በደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት በደረሰው የጎርፍ አደጋ ለተጎጅዎች የሚሆን የውጭ እርዳታ መግባት ጀምሯል፡፡

በደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት በደረሰው የጎርፍ አደጋ ለተጎጅዎች የሚሆን የውጭ እርዳታ መግባት ጀምሯል፡፡rnrnበሞዛምቢክ፣ ማላዊ እና ዚምባቡዌ ከባድ አውሎ ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ቁጥራቸው 3 መቶ የሚደርሱት ሲሞቱ ከ2.6 በላይ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው ተሰደዋል፡፡rnrnየተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአደጋው ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉት ነዋሪዎች የእለት ደራሽ እርዳታ እንዲደረግላቸው በጠየቀው መሰረት የተለያዩ ሀገራት ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡rnrnአልጀዚራ እንደዘገበው የመንግስታቱ ድርጅት ለተጎጂዎቹ 20 ሚሊዮን ዶላር በመለገስ ድጋፉን ከራሱ ጀምሯል፡፡rnrnየአውሮፓ ህብረትም 3.9 ሚሊዮን ዶላር በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች አንዲሰጥለት ፈቅዷል ነው የተባለው፡፡ የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ የ350 ሺህ ዶላር ድጋፍ ሰጥቷል፡፡rnrnከዓለም እና አህጉር አቀፍ ተቋማቱ በተጨማሪ ሀገራት በተናጠል ለአደጋው ተጋላጮች የእርዳታ እጃቸውን እየዘረጉ መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል፡፡rnrnእንግሊዝ ከ7 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለመርዳት ቃል ስትገባ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች 4.9 ዶላር ለመስጠት ማሰቧን ኤሜሬትስ የዜና ወኪል በዘገባው አስነብቧል፡፡rnrnየጎረቤት ታንዛንያ መከላከያ ተቋም ደግሞ 238 ቶን ምግብ እና መድሃኒት ለተፈናቃዮቹ እንዲጓጓዝ አድርጓል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Africa