በኮንጎ ታሪክ የመጀመሪያው ተቃዋሚ ፕረዝዳንት ሆነው ተመረጡrnrnየጆሴፍ ካቢላ መንግስት ከአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ስልጣን ለመጋራት ድርድር ላይ ነው በተሰማ ወሬ ከምርጫ ውጤት በኋላ ብጥብጥ እንዳይነሳ ስጋትን ፈጥሮ ነበር፡፡rnrnበዚህም የተነሳ በኮንጎ የምርጫ ውጤት በሚገለፅበት ዋዜማ አድማ በታኝ ፖሊሶች በተጠንቀቅ ላይ ነበሩ፡፡rnrnዛሬ ማለዳ ይፋ በሆነው የምርጫ ውጤት ተቃዋሚው ፌሊክስ ሲሴኪንዲ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ለመሆን የሚያስችላቸውን ድምፅ በማግኘ አሸናፊናታቸው ታውቋል፡፡rnrnከተቃዋሚ ፓርቲዎቹ መካከል ለአሸናፊነት ትልቅ ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩት ማርቲን ፋዩሉ ግን ውጤቱን ውድቅ አድርገውታል፡፡rnrnሲሴኪንዲ ከ7 ሚሊዮን በላይ ድምፅ ሲያገኙ ፋዩሉ ከ6.4 ሚሊዮን ያልዘለለ ድምፅ ነው ያገኙት ተብሏል፡፡rnrnየፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላን ፓርቲ ወክለው የተወዳደሩት ኢማኑኤል ራማዛኒ ሻዳሪ ደግሞ ያገኙት ድምፅ አምስት ሚሊዮን አይሞላም፡፡rnrnአንዳንድ የምርጫ ታዛቢዎች የምርጫ ሂደቱ በርካታ እንከኖች ታይተውበታው እንደነበር ከውጤቱ ቀደም ብለው አመላክተዋል፡፡rnrnለአብነትም አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ዘግይተው መከፈታቸው እና ቀድመው መዘጋታቸው እንዲሁም የምርጫውን ውጤት የሚቆጣጠሩ ማሺኖች የማይሰሩባቸው ጣቢያዎችም ነበሩ ብለዋል በሪፖርታቸው፡፡rnrnዲሞክራቲክ ኮንጎ ከ59 ዓመት በኋላ የመጀመሪያውን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ብታካሂድም ውጤቱ በካቢላ መንግስት እና በአሸናፊው ጋት የሲሴኪንዲ ፓርቲ መካከል አሻጥር ሳይኖርበት አይቀርም የሚል ስጋት አማሳደሩ አልቀረም፡፡rnrn





