Arts TVArts TV
← NewsAfrica

በካርቱም የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አልደገፉም የተባሉ አንድ የሃይማኖት አባት ከመስጊድ ተባረሩ

Arts TV · ጃን 14 2019

በካርቱም የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አልደገፉም የተባሉ አንድ የሃይማኖት አባት ከመስጊድ ተባረሩ

በካርቱም አንድ የሀይማኖት አባት በሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ባለመደገፋቸው ህዝቡ ከመስጊድ አባርሯቸዋል ተባለ ።rnrnሱዳን ውስጥ ካሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀይማኖታዊ መሪዎች አንዱ የሆኑት ኢማም አብዱል ሀይ ዩሱፍ  ተቃውሟውን  እየመሩ አይደለም በሚል ከአማኞች በቀረበባቸው  ውንጀላ  ነው ከመስጊድ  የተባረሩት።rnrnበማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በተለቀቀ ተንቀሳቃሽ ምስል፤ መንግሥትን በመደገፍ የሚታወቁትን  እኚህን ኢማም አንድ ግለሰብ ሲቆጣቸው ታይቷል።rnrnሮይተርስ እንደዘገበው ባለፈው አርብ ዕለት ከስግደት በኋላ የአልበሽር አገዛዝ መውደቅ አለበት የሚል ተቃውሞ ተነስቶ አስለቃሽ ጭስ ተጠቅመው ፖሊሶች ሰልፉን በትነውታል።rnrnየሱዳን ተቃውሞ የተቀጣጠለው መንግሥት በነዳጅና በዳቦ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉን ካስታወቀ በኋላ ሲሆን ባለፉት ሦስት ሳምንታት 22 ሰዎች መገደላቸውም የሚታወስ ነው።

More in Africa