Arts TVArts TV
← NewsHealth

በኢትዮጵያ ከሚገኙ የጤና ተቋማት ውስጥ 62 በመቶ የሚሆኑን በዳታ ቤዝ የማስተሳሰር ስራ ተጠናቀቀ

Arts TV · ዲሴም 28 2018

በኢትዮጵያ ከሚገኙ የጤና ተቋማት ውስጥ 62 በመቶ የሚሆኑን በዳታ ቤዝ የማስተሳሰር ስራ ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ከሚገኙ የጤና ተቋማት ውስጥ 62 በመቶ የሚሆኑን በዳታ ቤዝ የማስተሳሰር ስራ ተጠናቀቀ

rnአርትስ ታህሳስ 19 2011rnrnእንደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገለጻ የጤና ተቋማቱ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን እንዲከተሉ እና በመረጃዎች እንዲተሳሰሩ  የማድረግ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።rnrnሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን መረጃን ከማዘመን ጋር ተያይዞ ዲጂታላይዝ እንዲሆኑ ወይም ዘመናዊ አያያዝ እንዲኖራቸው ማድረግ ፣ የመረጃን አጠቃቀም ማሳደግ እና የተቋማቱን አመራር የማስተካከል ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።rnrnይህ አሰራር የዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ተግባራዊነትን ውጤታማ የሚያደርግ በመሆኑ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራበት ነው ብለዋል፡፡rnrnሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን እንዳሉት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተደረሰ ስምምነት ጤና ተቋማቱ በኢንተርኔት የማስተሳሰር እና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ተግባራዊ  እየተደረገ ነው።rnrnይህም ከካርድ ጀምሮ ሌሎች የህክምና አገልግሎቶች ዲጂታል እንዲሆኑ ከዚህ ቀደም ይሰራበት የነበረውን ማኑዋል በማስቀረት ተግባር አንዱ የህክምና ክፍል ውስጥ ያለ መረጃ ሌሎቹም የተቋሙ ክፍሎች ውስጥ በተመሳሳይ ጊዜ እንዲደርሱ ማድረግ ተችሏል።rnrnይህ ተግባራዊ እንዲሆን ከተደረገባቸው ጤና ተቋማት ውስጥ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንዱ ነው።rnrnበሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም  የህክምና ካርድ ከማውጣት ጀምሮ ሌሎች የህከምና አገልግሎቶቹን ለማግኘት መረጃ የሚያዘው በወረቀት ላይ ነበር።  ይህ አሰራር ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ ግን የታካሚው መረጃ ዘመናዊ ሆኗል ፋና እንደዘገበው።

More in Health