በኢትዮጵያ በየዓመቱ ህይወታቸውን ከሚያጡት ሰዎች መካከል ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ምክንያት ነው ተባለ
rnአርትስ 30/03/2011rnrn rnrn ከነዚህም መካከል ካንሰር፣ የስኳር ህመም እና ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ ህመሞች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡ rnrnበአሁኑ ሰዓት 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የስኳር ህመም ያለባቸው ሲሆን 16 በመቶ ያህል አዋቂዎች የደም ግፊት ህመም እንዳለባቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የአመጋገብ እና የአኗኗር ዘይቤ መቀየር ለችግሩ መስፋፋት ጉልህ ድርሻ አበርክቷል፡፡ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ዋነኛ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ rnrnጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል በየወሩ የተመረጡ መንገዶችን ከተሸከርካሪ ፍሰት ነጻ በማድረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን የማድረግ መርሃ ግብር ጀምሯል፡፡ rnrn በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚያገለግሉት ዶክተር ምትኩአዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ አብዛኞቹን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከል ይቻላል ብለዋል፡፡ rnrnአርትስ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎችም እንዲህ አይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ መልካም መሆኑን ተናግረው ቀጣይነት እንዲኖረው ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ rnrnበየወሩ ከሚካሄደው መርሃ ግብር ጎን ለጎን የጡት ካንሰር፣ የስኳር እና የደም ግፊት ነጻ የምርመራ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ይህም ህመሙ ሳይባባስ አስፈላጊውን ህክምናና ጥንቃቄ ለማድረግ ይረዳል ነው ያሉት ዶክተር ምትኩ፡፡rnrn






