Arts TVArts TV
← NewsAfrica

በአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎች የኢትዮጵያን ጥቅም ያስከበሩ መሆናቸው ተገለጸ

Arts TV · ፌብ 13 2019

በአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎች የኢትዮጵያን ጥቅም ያስከበሩ መሆናቸው ተገለጸ።rnrnኢትዮጵያ በቅርቡ ያጸደቀችው የስደተኞች አዋጅም በህብረቱ አባል ሃገራት ዘንድ አድናቆት ተችሮታል።rnrnማክሰኞ የካቲት 4 ቀን በተጠናቀቀውና ''ዘላቂ መፍትሄ በአስገዳጅ ሁኔታ ለሚፈናቀሉ የአፍሪካ ስደተኞች፣ ከስደት ተመላሾች እና የውስጥ ተፈናቃዮች'' በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት በተካሄደው 32ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ያስጠበቁ ነበሩ ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ  ።rnrnየአፍሪካን አህጉር ህዝቦች መፃዒ እድል የሚወስኑ በርካታ ውሳኔዎች ተላልፈውበታል በተባለው በዚሁ ጉባዔ ላይ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች የኢትዮጵያን ጥቅም ያስጠበቁ እንዲሆኑ በአገራችን በኩል ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራ ተስርቷል ብሏል ቃል አቀባዩ። በዚህም አመርቂ ውጤት ተገኝቷል ነው ያለው።rnrnበጉባኤው ከተወሰኑ ውሳኔዎች መካካል የሰው ሃይል ሪፎርም አንዱ ሲሆን የሪፎርሙ አካል የነበረው የሰው ሃይል ቅጥር የየአገሮችን ኮታ መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲሻሻል የሚለው አንቀጽ ጸድቋል ተብሏል።rnrnይህ ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቶ መጽደቁ በአሁኑ ወቅት በህብረቱ ውስጥ በአስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ በሎካል መደብ ላይ እየሰሩ ያሉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች ሳይፈናቀሉ እንዲቀጥሉ አስችሏል።rnrnበቀጣይ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በዚሁ ዘርፍ በአፍሪካ ህብረት ውስጥ የስራ እድል እንዲያገኙ አስተማማኝ መሰረት ለመጣልም አስችሏል ተብሏል። በተያያዘ ዜናም ኢትዮጵያ ያጸደቀችው የስድተኞች አዋጅ በመሪዎቹ ጉባኤ አድናቆት ተችሮታል።rnrnጉባኤው በሪፖርቱ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያፀደቀችው አዲሱ የስደተኞች አዋጅ ወቅቱን ያገናዘበና ለአፍሪካ ብሎም ለመላው ዓለም በሞዴልነት የሚወሰድ ነው ብሎታል።rnrnየተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒ ጎቶሬስን ጨምሮ በርካታ መሪዎች ባደረጉት ንግግር አዲሱ አዋጅ የስደተኞቹን ኑሮ ለማሻሻል ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ኢትዮጵያን ያስመስግናታል ብለዋል።rnrnኢትዮጵያ ከ900,000 በላይ ስደተኞችን በመቀበል ከዩጋንዳ በመቀጠል ከአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

More in Africa