በአርሲ ዩኒቨርሲቲ በኢንተርን ሀኪሞች ላይ የደረሰውንጉዳት እንዳሳዘነዉ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡rnrnበአገራችን እየተካሄደ ባለው ሁሉን አቀፍ ሪፎርም ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ ጀምሮ የተለያዩ ሰብአዊና ህጋዊ መብቶች እንዲከበሩ መንግስት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል::rnrnየህክምና ባለሙያዎች እንደማንኛውም ግለሰብና ባለሙያ ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የማቅረብ መብት እንዳላቸው በጽኑ ይታመናል ብሏል የጤና ሚኒስቴር ፡፡rnrnየጤና ሚኒስትሩ በትላንትናዉ እለት በአርሲ ዩኒቨርስቲ ኢንተርን ሀኪሞች ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ለዩኒቨርስቲው አመራሮች ለማቅረብ በወጡበት ወቅት በአከባቢው የሚገኘው ስርዓት አስከባሪ የኃይል እርምጃ በመውሰድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ከደረሰን ሪፖርት መረዳት ተችሏል ብሏል::rnrnበደረሰው ጉዳት የጤና ሚኒስቴር እጅጉን ያዘነ ስሆን ይህንን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል::rnrnጉዳቱን ያደረሱ አካላትም በአስቸኳይ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ተገቢው ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እየሰራ ይገኛል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
← NewsHealth
በአርሲ ዩኒቨርሲቲ በኢንተርን ሀኪሞች ላይ የደረሰውንጉዳት እንዳሳዘነዉ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
Arts TV · ኤፕሪ 18 2019





