Arts TVArts TV
← NewsAfrica

በምስራቃዊ  የኮንጎ ግዛት የተከሰተውን የኢቦላ ቫይረስ ተቆጣጥሬያለሁ ሲል የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

Arts TV · ፌብ 22 2019

በምስራቃዊ  የኮንጎ ግዛት የተከሰተውን የኢቦላ ቫይረስ ተቆጣጥሬያለሁ ሲል የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

በምስራቃዊ  የኮንጎ ግዛት የተከሰተውን የኢቦላ ቫይረስ ተቆጣጥሬያለሁ ሲል የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡rnrnበዴሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ  የኢቦላ ቫይረስ በሰፊው ከተሰራጨባቸው አካባቢዎች የምስራቃዊ ኮንጎ ግዛት ዋነኛው ቢሆንም በዚሁ አካባቢ ያለውን ስርጭት መግታት መቻሉን ነው የሀገሪቱ ጤናጥበቃ ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡rnrnሚኒስቴር መስሪያቤቱ በኒ በተባለውና ቫይረሱ በስፋት ተሰራጭቶበት በነበረው የሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ባለፉት 21 ቀናት አዲስ ህሙማን ያለመመዘገቡን ገልጿልrnrnበሌላ በኩል ቡተምቦና ካትዋ በተባሉ ቦታዎች ባለፉት ሶስት ሳምንታት 74 ህሙማን መመዝገባቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡rnrnሲጂቲኤን እንደዘገበው ሀገሪቱ ከቫይረሱ ስርጭት ነፃ ሆናለች የሚለውን ለማወጅ ለ42 ተከታታይ ቀናት አዳዲስ ህሙማን ሳይመዘገቡ መቆየት አለባቸው፡፡rnrnከህሙማኑ መካከል 528 ህይወታቸው ማለፉም ነው የተነገረው፡፡rnrnበሀገሪቱ ያለው የሰላም ሁኔታ የቫይረስ ስርጭቱን ለመከላከል ሀገሪቱ የምታደረገው እንቅስቃሴ  ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ ይነገራል፡፡rnrnበግዛቱ ተሰራጭቶ በነበረው በዚሁ የኢቦላ ቫይረስ  ከ500 በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡ ዘገባው የሲጂቲኤን ነው፡፡rnrn rnrn rnrn rnrn rnrn 

More in Africa