Arts TVArts TV
← NewsAfrica

በማሊ የሰላም አስከባሪ ሀይሎች ላይ ጥቃት ደረሰ

Arts TV · ጃን 21 2019

በማሊ የሰላም አስከባሪ ሀይሎች ላይ ጥቃት ደረሰ

በማሊ የሰላም አስከባሪ ሀይሎች ላይ ጥቃት ደረሰrnrnኪዳል ከተባለችው የማሊ ክልል በ200 ኪሎሜትር  ርቀት ላይ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይሎች ካምፕ ላይ ነው ጥቃቱ የተፈፀመው፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በጥቃቱ 10 የቻድ ወታደሮች ህይዎታቸው ሲያልፍ ሌሎች 25 ወታደሮች ደግሞ ቆስለዋል፡፡rnrnየመንግታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በረቀቀ መንገድ ጥቃቱን ያደረሱት አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ብለዋል፡፡rnrnአልቃኢዳ ኢን ኢስላሚክ መግረብ የተሰኘው ቡድን ጥቃቱን ያደረስኩት እኔ ነኝ በማለት  ሀላፊነቱን መውሰዱን የሞሪታኒያው አል አክባር የዜና ወኪል በዘገባው አስነብቧል፡፡rnrnቡድኑ ይህን ጥቃት ለማድረስ ምክንያት የሆነውም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒሰትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ለጉብኝት ቻድ መግባታቸው መሆኑን ቡድኑ ይፋ አድርጓል፡፡rnrnየተባበሩት መንግስታት ድርጅት በማሊ 1 ሺህ 200 የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ያሰማራ ሲሆን ሀገሪቱ ለሰላም አስከባሪ ሀይሎች እጅግ አደገኛ ከሚባሉት ሀገራ በቀዳሚነት ትገኛለች፡፡rnrnምክንያቱ ደግሞ ማሊ ውስጥ አልቃኢዳ እና አይ ኤስ አይ ኤስን  ጨምሮ በርካታ ታጣቂ ቡድኖች በስፋት የሚገኙ መሆናቸው ነው፡፡rnrn 

More in Africa