Arts TVArts TV
← NewsHealth

በማህበረሰብ አቀፍ የኤች.አይ.ቪ ተጽእኖ ላይ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ይፋ ሆነ

Arts TV · ዲሴም 11 2018

በማህበረሰብ አቀፍ የኤች.አይ.ቪ ተጽእኖ ላይ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ይፋ ሆነ

በማህበረሰብ አቀፍ የኤች.አይ.ቪ ተጽእኖ ላይ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ይፋ ሆነ

rnአርትስ 02/04/2011rnrnጥናቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ባሉ ከተሞች ዕድሚያቸው ከ15-64 ዓመት ከሆኑትና ኤች.አይ.ቪ ካለባቸው ሰዎች ውስጥ 70% የሚሆኑት  የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መቀነሱን አሳይቷል፡፡rnrnነገርግንዕድሜያቸውከ15-64 ዓመትየሆኑኤች.አይ.ቪበደማቸውካለባቸውወንዶችውስጥኤች.አይ.ቪእንዳለባቸውየሚያውቁትከሁለትሶስተኛበታች (62%) ናቸው ብሏል፡፡rnrnበጥናቱ ይፋዊ ስነ-ስርዓት የተገኙት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ  ዶ/ር አሚር አማን እንደተናገሩት ባለፉት አስራ ሰባት ዓመታት በኤች.አይ.ቪ መከላከልና መቆጣጠር ላይ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመው ቀደም ሲል በየዓመቱ በቫይረሱ ይያዙ ከነበሩት 81 ሺህ ሰዎች አሁን ላይ ወደ 15 ሺህ ዝቅ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔውም ከነበረው 5.8% ወደ 0.9% ማውረድ የተቻለ ቢሆንም አሁንም ችግሩ አሳሳቢ ስለሆነ ባለፉት ዓመታት በተገኙ ውጤቶች ሳንዘናጋ ልዩ ትኩረት ሰጥተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡rnrnጥናቱ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስተባባሪነትና በአሜሪካ ፕሬዝዳንት አስቸኳይ ጊዜ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዕቅድ የገንዘብ ድጋፍ የተካሄደ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጠቁሟል፡፡rnrn

More in Health