<strong>ምንጋግዋ ፑቲንን ሀገሬን ለማልማት ቀኝ እጅዎን ያውሱኝ እያሏቸው ነው፡፡</strong>rnrnየዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የፑቲንን ድጋፍ ፍለጋ ባለስልጣኖቻቸውን አስከትለው ሞስኮ ገብተዋል፡፡rnrnበሀገር ቤት በዋጋ ንረት ሳቢያ የተቃውሞ ሰልፍ ረፍት የነሳቸው ምናጋግዋ ክሬምሊን ከገቡ በኋላ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ሀገሬ ከኢኮኖሚ ችግር ትላቀቅ ዘንድ እንደታላቅ ወንድም አቅፈው ደግፈው እንዲያግዙኝ አፈልጋለሁ ብለዋቸዋል፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ኤመርሰን ምናንጋግዋ ሩሲያን ጨምሮ አምስት ሀገራትን ለመጎብኘት እቅድ ይዘው ነው ከሀራሬ የወጡት፡፡rnrnየሩሲያው ጉብኝት ዋነኛ ዓላማ በዚምባቡየ የተከሰተውን የኢኮኖሚ አለመገረጋጋት ፈር ለማስያዝ የቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ለማግባባት ነው ተብሏል፡፡rnrnምናንጋዋ ከፑቲን ጋር ሲወያዩ የሀራሬ እና የሞስኮ ግንኙነት በፖለቲካው መስክ የተዋጣለት ስለመሆኑ አልጠራጠርም የኢኮኖሚው ዘርፍ ግን ብዙ ስራ ይጠይቃል፤ ለዚህም የታላቅ መድሜ ፑቲን ድጋፍ እንደማይለየኝ እተማመናለሁ ብለዋል፡፡rnrnፑቲን በበኩላቸው ለጀመሪያ ጊዜ ክሬምሊን የተገኙትን ምናንጋግዋን እንኳን ደህና መጡ ካሉ በኋለ መንግስታቸው ለዚምባብዌ ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠውላቸዋል፡፡rnrnሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ውይይት በሀገራቱ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ጥሩ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከክሬምሊን የወጣ መረጃ ያመላክታል፡፡rnrnፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ባለፈው ዓመት ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ሀገሪቱን የመሩትን የቀድሞ አለቃቸውን ሮበርት ሙጋቤን አስወግደው ስልጣን ከያዙ ጀምሮ ተፈላጊውን ለውጥ ማምጣት ተስኗቸዋል እየተባሉ ይተቻሉ፡፡





