Arts TVArts TV
← NewsSocial

204 ማዳበሪያ ጅሶ፣ገለባና ሰጋቱራ የተቀላቀለበት ዱቄት በእህል በረንዳ ተያዘ፡፡

Arts TV · ሜይ 28 2019

204 ማዳበሪያ ጅሶ፣ገለባና ሰጋቱራ የተቀላቀለበት ዱቄት በእህል በረንዳ ተያዘ፡፡

204 ማዳበሪያ ጅሶ፣ገለባና ሰጋቱራ የተቀላቀለበት ዱቄት በእህል በረንዳ ተያዘ፡፡rnrnበአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እህል በረንዳ በሚገኙ 2 የገበያ አደራሾች ውስጥ ነዉ 204 ማዳበሪያ ጅሶ፣ገለባና ሰጋቱራ የተቀላቀለበት ዱቄት የተያዘዉ፡፡ የአካባቢዉ ነዋሪዎች "የከተማችንን ቆሻሻ እናፅዳ እያልን ባለንበት ባሁኑ ወቅት አፀያፊ ተግባር ላይ የተሰማራውን የቆሸሸ አዕምሮንም ማፅዳት ይኖርብናል" ብለዋል፡፡rnበአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እህል በረንዳ ምዕራብ እና ግንባታ የገበያ አዳራሽ አከሲዮን ማህበር ሱቆች ውስጥ ነው ዱቄቱ ተከማችቶ የተገኘው፡፡rnየተፈፀመው ድርጊት በየትኛውም እምነት አፀያፊ መሆኑን የተናገሩት የእህል በረንዳ ነጋዴዎች፣ ሸማቾች እና ነዋሪዎች ደርጊቱን የፈፀሙ ግለሰቦች ለህግ ቀርበው አሰተማሪ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቀዋል፡፡

More in Social