Arts TVArts TV
← NewsEconomy

10 ሚሊዮን ብር የሚገመት ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Arts TV · ኤፕሪ 8 2019

10 ሚሊዮን ብር የሚገመት ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

10 ሚሊዮን ብር የሚገመት ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉrnrnያቤሎ፣ ሀረርና ጅግጅጋ አካባቢዎች ግምታዊ ዋጋው 10 ሚሊዮን ብር የሆነ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በፌዴራል ፖሊስና በጉምሩክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡rnያቤሎ አካባቢ 9.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ መድኃኒት፣ ስኳርና ሌሎች ዕቃዎችን በተሸከርካሪዎች ሲጓጓዝ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡rnrnከዚሁ ጋር በተያያዘ ሦስት ግለሰቦች ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ የሞያሌ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ቅርንጫ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡rnየገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ ግምታዊ ዋጋቸው 520 ሺህ ብር የሚደርስ የግንባታ ብረትና ምግብ ነክ የሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ወደ ጅግጅጋ እና ሀረር ለማስገባት ሲሞከር በፌዴራል ፖሊስ አባላትና በጉምሩክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

More in Economy