Arts TVArts TV
← NewsSocial

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ሊወያዩ ነው

Arts TV · ኤፕሪ 30 2019

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ሊወያዩ ነው።rnrnጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመላው ሀገሪቱ ከተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ጋር ሊወያዩ ነው ።rnrnጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከጤና ባለሙያዎች ጋር የሚያደርጉት ውይይትም የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 26 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን  በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።rnrnበጤና ባለሙያዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደመወዝን ጨምሮ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ላይ እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን ፥ ውይይቱም በጥያቄዎቹ ላይ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል።rnrnየጤና ሚኒስትሩ እንዳስታወቁት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱት የውይይት መድረኮች የመፍትሄ ሃሳቦች ለማስቀመጥ የሚያስችሉ ናቸው  ብለዋል።

More in Social