ግምታዊ ዋጋቸው ከ1.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉrnrnስምንት መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ አርባ (867,040) ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎችን ከአሮጌ ብረታ ብረት ጋር ኮድ 3- A30745 አአ በሆነ FSR ተሸከርካሪ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞከር በጉምሩክ ስራተኞች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ አልበረከቴ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ ተይዟል፡፡ በወቅቱ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘው አስፈላጊው የማጣራት ስራ እየተሠራ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው፡፡rnrnበተያያዘ ዜና መጋቢት 15/2011 ጨለማን ተገን በማድረግ ኮድ 2 96913 አአ የሚል የሀሰት ታርጋ የለጠፈ ቪትዝ ተሸከርካሪ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል ቶጎጫሌ መስመር በቁጥጥር ስር መዋሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ኮድ3-05607 ሱማ ሻምፖ ተሸከርካሪም 750 ሺ ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው 1250 ጀሪካን ባለ 20 ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ጅግጅጋ ሲገባ ቀብሪበያሕ መስመር በፌደራል ፖሊስ አባለት፣ በአድማ ብተናና በጉምሩክ አባላት መያዙን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገልጿል፡፡rnrnኮንትሮባንድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይም ሆነ በህበረተሰቡ ጤና ላይ የሚደርሰው ጉዳት የከፋ በመሆኑ ህበረተሰቡ ኮንትሮባንዲስቶችን በማጋለጥ ከምንጊዜውም በተሻለ መልኩ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡rnrnምንጭ ገቢዎች ሚኒስቴርrnrn rnrn
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
ግምታዊ ዋጋቸው ከ1.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
Arts TV · ማርች 25 2019

More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019

